የፍትሕ ሚኒስቴር ተቋማዊ ለውጥ ማምጣቱን አስታወቀ
አዲስ አበባ, ጥቅምት 15 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) -

የፍትሕ ሚኒስቴር ያሉበትን የአሰራር፣ የአደረጃጀትና የሰው ኃይል ችግሮች አስወግዶ ተቋማዊ ለውጥ በማምጣት ከመንግሥትና ከሕዝብ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑን የፍትሕ ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም የዳኝነት ሚኒስቴር ተብሎ የተቋቋመበትን 100ኛ አመት ምክንያት በማድረግ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የሚኒስቴር መሥሪያቤቱን ቀደም ሲል በሚኒስትርነት ያገለገሉ በተገኙበት የሚኒስቴሩ ሠራተኞች በአዲሱ ሚሌኒየም ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ሕብረተሰቡን ለማገልገል ቃል ገብተዋል፡፡

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አላስፈላጊና ድግግሞሽ የሚታይባቸውን የሥራ ክፍሎች ሰርዞ ወጪን በመቀነስና የተጀመረውን የተቋማዊ ለውጥ ሥራ በሚመራ አዲስ ኃይል በመተካት የሥራ ቅልጥፍና ለማምጣት መቻሉን ሚኒስትሩ አቶ አሰፋ ከሲቶ በዚሁ ጊዜ ተናግረዋል፡፡

ከክልሎች ፍትሕ ቢሮዎች፣ ከምርመራና ከዳኝነት አካላት ጋር የሚያገናኝና የክትትልና ቁጥጥር ሥራ የሚያከናውን ማስተባበሪያ በመቋቋሙ የሥራ ቅልጥፍናና ጥራት ለማምጣት ተችሏል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ እንዳሉት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ እና ከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ፣ አዲስ አበባና ድሬዳዋ ምድቦች የወንጀል ምርመራና ድጋፍ ዓቃቤ ሕግ ቡድን በመቋቋሙ ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት የወንጀል ምርመራ ሥራን ለመደገፍና ለመከታተል ተችሏል፡፡

ከ100 ሺህ በላይ የነበረው የወንጀል ምርመራ መዝገብ ውዝፍ አሁን ወደ 10 ሺህ የወረደ መሆኑንና የዓቃቤ ሕግ መዝገብ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ መቻሉን፣ እንዲሁም ዓቃብያነ ሕግን መገምገም የማይታሰብ የነበረ ሲሆን ተከታታይ ግምገማ በማካሄድ ችግሮችን መለየት፣ መፍትሔዎችን መፈለግና ችግር ፈጣሪዎች በሆኑት ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መውሰድ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ከአመለካከት ችግር የተነሳ ዓቃብያነ ሕግንና ዳኛን ማገናኘት የማይቻል የነበረ ቢሆንም ከጠቅላይ ፍርድ ቤትና ከአቅም ግንባታ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሁሉኑም ዳኞችና ዓቃብያነ ሕግ በአንድ ላይ በመንግስት ፖሊሲዎች፣ ስትራተጂዎችና በሕገመንግስቱ ላይ የአንድ ወር ሥልጠና ለመስጠት መቻሉን አመልክተዋል፡፡

በፈርድ ቤት ቅጣት የተወሰነባቸው ታራሚዎች አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተው ሲገኙ ይቅርታ የሚያገኙበት ሥርአት ተዘርግቶ በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውንና በተለይ በ1998 እና 1999 ዓ.ም ብቻ ከመላ አገሪቱ በትንሹ 30 ሺህ የሚሆኑ ታራሚዎች ይቅርታ አግኝተው ከእስር መለቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡

ሪሪ11፡20 የ12፡33

---END---

Headlines
ኤች አር 2003 ለኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባታ የሚፈይደው አንዳችም ጠቀሜታ የለውም፤ በየደራጃውም ሊወገዝ ይገባል
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሶማሊያን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓሊ መሐመድ ጌዲን አነጋገሩ
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሽብርተኝነት ለሰው ዘር ጠንቅ በመሆኑ ሊወገድ ይገባዋል ሲል ጥሪ አስተላለፈ
የቼክና የስሎቫክ ስድስት አገር አሳሾች በሕይወት መግኘት የሚያስደስት ነው
የቼክ ፕሬዚዳንት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በድጋሚ መመረጣቸውን በማስመልከት የደስታ መግለጫ አስተላለፉ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሹመት ሰጡ
ሰዓሊዋ በኢትዮጵያ ያደረገችው ቆይታ እንዳስደሰታት ገለጸች
ዩኒቪርሲቲው አዲስ ፋኩሊቲዎች ከፈተ
በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከ632 ነጥብ 6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደአገር ቤት ልከዋል
በቤተሰብ የውሃ አሰተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ የሚነጋገር ዓለም አቀፍ ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል
ድርጅቱ ሞዴሎችን በመምረጥ የፋሽን ትርዒት ሊያቀርብ ነው
የመድሀኒት አስተዳዳርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአንድ የአሜሪካ ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
በኦሮሚያ ክልል ባለፈው የምርት ዘመን 152 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገንቷል፡፡
ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ባህልና ሐይማኖት በተከተለ ሁኔታ የሚሌኒየም በዓላቸውን እያከበሩ ናቸው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ
የፍትሕ ሚኒስቴር ተቋማዊ ለውጥ ማምጣቱን አስታወቀ
ቆነጃጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ
በልመና የተሠማሩ ሰዎች ወደመኖሪያቸው እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ አርቲስቶች ገለጹ
ባለስልጣኑ የአደገኛ መድሀኒቶችና እጾች ህገወጥ ዝውውርና አጠቃቀምን ለመከላከል የአምስት ዓመት እቅድ አዘጋጀ
በትግራይ ክልል ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ 117ሺህ ሕጻናት ትምህርት ጀመሩ
በአርሲ ምርጥ ዘር በማባዛት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች እስከ 30 ሺህ ብር ድረስ ገቢ እያገኙ ነው
(c) The Ethiopian News Agency