አዲስ አበባ, ጥቅምት 15 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - በሚስ ቱሪዝም ሚሌኒየም የቁንጅና ውድድር ላይ ለመካፈል ከመላው ዓለም የተሰባሰቡት ቆነጃጅት ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ።የኢትዮጵያን ሚሌኒየም አስመልክቶ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የቁንጅና ውድድር ላይ የሚሳተፉት እነዚሁ ቆነጃጅት ዛሬ ከረፋዱ ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድን የተለያዩ የስራ ክፍሎች ጎብኝተዋል።
ቆነጃጂቱ በተለይ የአየር መንገዱን የአውሮፕላን ሞተርና አካል ጥገናና ማሰልጠኛ ማዕከልን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ከ36 የተለያዩ የዓለም አገራት የተውጣጡት እነዚሁ ቆነጃጅት ትላንት በእንጦጦ ተራራ ላይ የችግኝ ተከላ ማከናወናቸው ይታወሳል።
---END---