የቼክና የስሎቫክ ስድስት አገር አሳሾች በሕይወት መግኘት የሚያስደስት ነው
አዲስ አበባ, ጥቅምት 15 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - በደቡብ ኢትዮጵያ አገር ሲያስሱ በጫካ ውስጥ አድራሻቸውን ያጡት ስድስት ዜጎቻቸው በሕይወት መገኘት የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ጥረት ውጤት በመሆኑ እንዳስደሰታቸው የቼክና የስሎቫክ አገራት አምባሳደሮች ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ የቼክ ሪፑብሊክ አምባሳደር ዝዴኔክ ዲቢያሽና የስሎቫክ ሪፑብሊክ አምባሳደር ሚላን ሲጋኝ ከአሳሾቹ ጋር በመሆን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዛሬ እንደገለጹት ለዜጎቻቸው በሕይወት መገኘት የኢትዮጵያ መንግስትና የአካባቢው ነዋሪ ሕዝብ ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል፡፡

በዳንቺያ ወንዝ ላይ አገር ሲያስሱ አቅጣጫቸው የጠፋባቸው ሰዎችን ከአደጋ ለመታደግ ፈጣን እርምጃ በመውስድ አርዓያነት ያለው ተግባር የኢትዮጵያ መንግሰትና ሕዝብ በመፈጸማቸው ሁለቱም አምባሳደሮች አመስግነዋል፡፡

በተለይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስድስቱ አገር አሳሾች አቅጣጫ መሳትን ከሰማበት ወቅት አንስቶ የአደጋ ሰዎች በሄሊኮፕተር ወደአካባቢው ተደጋጋሚ በረራ በማድረግ ፍለጋው እንዲጠናከር ማድረጉ ትልቅ ተምሳሌት ነው ብለዋል፡፡

አገር አሳሾቹ በበኩላቸው የኦሞ ወንዝ ገባር በሆነውና በውብና ማራኪ አካባቢ ውስጥ በሚገኘው ዳንቺያ ወንዝ የመጀመሪያዎቹ አሳሽ መሆናቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡

ይሁንና የወንዙ አቅጣጫ በጀልባ ዘልቆ ለመዋኘት አስቸጋሪ ሥፍራ ላይ መድረሳቸውን እንዳረጋገጡ ወደኦሞ ወንዝ የሚያደርጉትን ጎዞ ለማቋረጥ መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡

ጥቅጥቅ ባለደን ውስጥ ደግሞ የከፋ አደጋ እንዳይገጥማቸው ወደቼክ ኤምባሲ በሳተላይት ሞባይል የድረሱልን ጥሪ ከሥፍራው ማስተላለፋቸውን ጠቁመዋል፡፡

ይሁን እንጂ የሻማ አካባቢ ነዋሪ ሕዝብ ፈጥኖ በመድረስ ከአስቸጋሪ ስፍራ እንደታደጋቸውና ምግብና ሌሎች ድጋፎችን በማቅረብ ፍቅር በተላበሰ እንክብካቤ ስላስተናገዳቸው አመስገነዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውብና ለቱሪስት አመቺ አገር መሆኗን አገር አሳሸሾቹ ገልጸው ሕዝቧም ለእንግዳ መልካም አቀባበል የሚያደርግና ጨዋ መሆኑን መስክረዋል፡፡

በስፍራው የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንደገለጹት በስድስቱ የቼክና የስሎቫክ ዜጎች በጥቅጥቅ ደን ውስጥ መሰወር ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትን በወቅቱ ማሳሰቡን ጠቁመው ሌት ተቀን በተደረገ ጥረት በአጭር ቀናት ውስጥ አድራሻቸው ሊግኝ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

አሳኞቹ አካባባቢውን በተመለከተ የተቀረጹትን የቪዲዮ ፊልሞች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ገጸበረከት ለመስጠት ፈቃደኛ በመሆናቸው አመስግነዋቸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሌላ አገር አሳሽ ቡድን ወደስፈራው በቅርቡ እንደሚንቀሳቀስ ከአምባሳደሮቹ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል፡፡

---END---

Headlines
ኤች አር 2003 ለኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባታ የሚፈይደው አንዳችም ጠቀሜታ የለውም፤ በየደራጃውም ሊወገዝ ይገባል
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሶማሊያን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓሊ መሐመድ ጌዲን አነጋገሩ
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሽብርተኝነት ለሰው ዘር ጠንቅ በመሆኑ ሊወገድ ይገባዋል ሲል ጥሪ አስተላለፈ
የቼክና የስሎቫክ ስድስት አገር አሳሾች በሕይወት መግኘት የሚያስደስት ነው
የቼክ ፕሬዚዳንት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በድጋሚ መመረጣቸውን በማስመልከት የደስታ መግለጫ አስተላለፉ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሹመት ሰጡ
ሰዓሊዋ በኢትዮጵያ ያደረገችው ቆይታ እንዳስደሰታት ገለጸች
ዩኒቪርሲቲው አዲስ ፋኩሊቲዎች ከፈተ
በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከ632 ነጥብ 6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደአገር ቤት ልከዋል
በቤተሰብ የውሃ አሰተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ የሚነጋገር ዓለም አቀፍ ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል
ድርጅቱ ሞዴሎችን በመምረጥ የፋሽን ትርዒት ሊያቀርብ ነው
የመድሀኒት አስተዳዳርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአንድ የአሜሪካ ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
በኦሮሚያ ክልል ባለፈው የምርት ዘመን 152 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገንቷል፡፡
ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ባህልና ሐይማኖት በተከተለ ሁኔታ የሚሌኒየም በዓላቸውን እያከበሩ ናቸው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ
የፍትሕ ሚኒስቴር ተቋማዊ ለውጥ ማምጣቱን አስታወቀ
ቆነጃጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ
በልመና የተሠማሩ ሰዎች ወደመኖሪያቸው እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ አርቲስቶች ገለጹ
ባለስልጣኑ የአደገኛ መድሀኒቶችና እጾች ህገወጥ ዝውውርና አጠቃቀምን ለመከላከል የአምስት ዓመት እቅድ አዘጋጀ
በትግራይ ክልል ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ 117ሺህ ሕጻናት ትምህርት ጀመሩ
በአርሲ ምርጥ ዘር በማባዛት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች እስከ 30 ሺህ ብር ድረስ ገቢ እያገኙ ነው
(c) The Ethiopian News Agency