በአርሲ ምርጥ ዘር በማባዛት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች እስከ 30 ሺህ ብር ድረስ ገቢ እያገኙ ነው
አሰላ, ጥቅምት 15 ቀን 2000 (አሰላ) - በአርሲ ዞን በሒጦሳ ወረዳ በምርጥ ዘር ማባዛት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች እስከ 30 ሺህ ብር ገቢ በማግኘት ተጠቃሚ መሆናቸውን የወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ጽሕፈት ቤት ገለጠ፡፡

የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አበራ ለማ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት ባለፈው ዓመት በወረዳው ከ600 የሚበልጡ አርሶ አደሮች የስንዴ፣ባቄላና አተር ምርጥ ዘር በማባዛት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

በወረዳው ከሶስት ዓመት በፊት በአነስተኛ የእርሻ መሬት ላይ የተጀመረው ምርጥ ዘር የማባዛት ስራ የአርሶ አደሩን ገቢ እያሳገ በመምጣቱ የተሳታፊ አርሶ አደሮች ቁጥር መጨመሩን ገልጠው ምርጥ ዘሩን ከአርሶ አደሩ የምርጥ ዘር ድርጅት ከአካባቢው ዋጋ 30 ብር ጭማሪ በማድረግ እንደሚረከብ አስታውቀዋል፡፡

በያዝነው የምርት ዘመን 607 አርሶ አደሮች በ490 ሔክታር መሬት ላይ ምርጥ ዘር በማባዛት ላይ መሆናቸውን አስታውቀው ከ18 ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ መገመቱንም ገልጠዋል፡፡

በልማቱ የተሳተፉ አርሶ አደሮች እንደየስራቸው ከአራት ሺህ እስከ 30 ሺህ ብር በነፍስ ወከፍ ገቢ ማግኘት እንደቻሉም አስታውቀዋል፡፡

ከተሳታፊዎቹ መካከልም አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ከምግብ ሰበል ጎን ለጎን ምርጥ ዘር በማባዛት ከፍተኛ ገቢ ማግኘት በመቻላቸው ከሳር ክዳን ቤት ወደ ቆርቆሮ መኖሪያ ቤት ከመሸጋገራቸውም ሌላ የንግድ ስራ የከፈቱም መኖራቸውን ገልጠዋል፡፡

ሪፖ 400 ኤዲ2 610

---END---

Headlines
ኤች አር 2003 ለኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባታ የሚፈይደው አንዳችም ጠቀሜታ የለውም፤ በየደራጃውም ሊወገዝ ይገባል
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሶማሊያን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓሊ መሐመድ ጌዲን አነጋገሩ
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሽብርተኝነት ለሰው ዘር ጠንቅ በመሆኑ ሊወገድ ይገባዋል ሲል ጥሪ አስተላለፈ
የቼክና የስሎቫክ ስድስት አገር አሳሾች በሕይወት መግኘት የሚያስደስት ነው
የቼክ ፕሬዚዳንት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በድጋሚ መመረጣቸውን በማስመልከት የደስታ መግለጫ አስተላለፉ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሹመት ሰጡ
ሰዓሊዋ በኢትዮጵያ ያደረገችው ቆይታ እንዳስደሰታት ገለጸች
ዩኒቪርሲቲው አዲስ ፋኩሊቲዎች ከፈተ
በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከ632 ነጥብ 6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደአገር ቤት ልከዋል
በቤተሰብ የውሃ አሰተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ የሚነጋገር ዓለም አቀፍ ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል
ድርጅቱ ሞዴሎችን በመምረጥ የፋሽን ትርዒት ሊያቀርብ ነው
የመድሀኒት አስተዳዳርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአንድ የአሜሪካ ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
በኦሮሚያ ክልል ባለፈው የምርት ዘመን 152 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገንቷል፡፡
ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ባህልና ሐይማኖት በተከተለ ሁኔታ የሚሌኒየም በዓላቸውን እያከበሩ ናቸው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ
የፍትሕ ሚኒስቴር ተቋማዊ ለውጥ ማምጣቱን አስታወቀ
ቆነጃጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ
በልመና የተሠማሩ ሰዎች ወደመኖሪያቸው እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ አርቲስቶች ገለጹ
ባለስልጣኑ የአደገኛ መድሀኒቶችና እጾች ህገወጥ ዝውውርና አጠቃቀምን ለመከላከል የአምስት ዓመት እቅድ አዘጋጀ
በትግራይ ክልል ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ 117ሺህ ሕጻናት ትምህርት ጀመሩ
በአርሲ ምርጥ ዘር በማባዛት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች እስከ 30 ሺህ ብር ድረስ ገቢ እያገኙ ነው
(c) The Ethiopian News Agency