በትግራይ ክልል ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ 117ሺህ ሕጻናት ትምህርት ጀመሩ
መቀሌ, ጥቅምት 15 ቀን 2000 (መቀሌ) - በትግራይ ክልል በያዝነው ዓመት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ 117 ሺህ ሕጻናት ትምህርት መጀመራቸውን የክልሉ ትምሀርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው የፕላንና ስታትስቲክስ ቡድን መሪ አቶ ገብረ መድህን መሰል ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት ህጻናቱ ትምህርት የጀመሩት በአዲሱ ሚሌኒየም ሰባት ዓመት የሞላቸውን ሕጻናት ትምህርት ቤት ለማስገባት በተደረገው ጥረት ነው፡፡

ክንውኑ ካለፈው ዓመት በ7 ሺህ ብልጫ እንዳለውና ውጤቱም ሊገኝ የቻለው ወላጆች፣መምህራንና የወረዳ መስተዳድር አካላት ባደረጉት እንቅስቃሴ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ሕጻናቱን ለማስተናገድ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ፣የመምህራን ቅጥርና ተጓዳኝ ሥራዎች መከናወናቸውን ቡድን መሪው አስታውቀዋል፡፡

ክልሉ በዚህ ዓመት ወደ ትምህርት ቤት ለማስገባት ካቀደው 88 በመቶው ያህል ማሳካቱንም ገልጸዋል፡፡

ኤዲ1 6 00 ኤዲ2 635

---END---

Headlines
ኤች አር 2003 ለኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባታ የሚፈይደው አንዳችም ጠቀሜታ የለውም፤ በየደራጃውም ሊወገዝ ይገባል
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሶማሊያን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓሊ መሐመድ ጌዲን አነጋገሩ
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሽብርተኝነት ለሰው ዘር ጠንቅ በመሆኑ ሊወገድ ይገባዋል ሲል ጥሪ አስተላለፈ
የቼክና የስሎቫክ ስድስት አገር አሳሾች በሕይወት መግኘት የሚያስደስት ነው
የቼክ ፕሬዚዳንት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በድጋሚ መመረጣቸውን በማስመልከት የደስታ መግለጫ አስተላለፉ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሹመት ሰጡ
ሰዓሊዋ በኢትዮጵያ ያደረገችው ቆይታ እንዳስደሰታት ገለጸች
ዩኒቪርሲቲው አዲስ ፋኩሊቲዎች ከፈተ
በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከ632 ነጥብ 6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደአገር ቤት ልከዋል
በቤተሰብ የውሃ አሰተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ የሚነጋገር ዓለም አቀፍ ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል
ድርጅቱ ሞዴሎችን በመምረጥ የፋሽን ትርዒት ሊያቀርብ ነው
የመድሀኒት አስተዳዳርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአንድ የአሜሪካ ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
በኦሮሚያ ክልል ባለፈው የምርት ዘመን 152 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገንቷል፡፡
ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ባህልና ሐይማኖት በተከተለ ሁኔታ የሚሌኒየም በዓላቸውን እያከበሩ ናቸው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ
የፍትሕ ሚኒስቴር ተቋማዊ ለውጥ ማምጣቱን አስታወቀ
ቆነጃጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ
በልመና የተሠማሩ ሰዎች ወደመኖሪያቸው እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ አርቲስቶች ገለጹ
ባለስልጣኑ የአደገኛ መድሀኒቶችና እጾች ህገወጥ ዝውውርና አጠቃቀምን ለመከላከል የአምስት ዓመት እቅድ አዘጋጀ
በትግራይ ክልል ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ 117ሺህ ሕጻናት ትምህርት ጀመሩ
በአርሲ ምርጥ ዘር በማባዛት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች እስከ 30 ሺህ ብር ድረስ ገቢ እያገኙ ነው
(c) The Ethiopian News Agency