አዲሰ አበባ, ጥቅምት 15 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - በኦሮሚያ ክልል ባለፈው የምርት ዘመን 6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሔክታር መሬት መልማቱን የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡የቢሮው ኃላፊ አቶ ድሪባ ኩማ ለትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት በምርት ዘመኑ በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማስመዝገብ በተደረገው ጥረት 152 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገንቷል፡፡
በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማስመዝገብ የግብዓብት ዝግጅት መደረጉን አመልክተው በዚሁ ወቅት በመንግገስት 1ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል ከተለያዮ የግል አቅራቢ ድርጅቶች ደግሞ ከ200 ሺህ ያላነሰ ማዳበሪያ መሰራጨቱን አመልክተዋል፡፡
በዚሁ ወቅት መንግስት ለክልሉ አርሶ አደሮች 140ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ማቅረቡንና አርሶ አደሩም በራሱ ማሳ ዘሮችን በማባዛት ለምርቱ እድገት አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልፀዋል፡፡
በዚሁ ወቅት የተለያዮ ሙያተኞችን በማሰልጠን ለስራ በማብቃትና ውጤታ እንዲሆኑ ተደርጓል ያሉት የቢሮው ሃላፊ ለ13 ሺህ 900 የልማት ሰራተኞችና የወረዳ ሙያተኞችን በአዲሱ የኤክስቴንሽንና ማሳ ዝግጅት ስራዎች ላይ ስልጠና ተሰጥተዋል ብለዋል፡፡
ከአራት ዓመት በፊት የክልሉ አጠቃላይ ምርት 48 ሚሊዮን ኩንታል እንደነበር አቶ ድሪባ አመልክተው ባለፉት አራት አመታት በተደረገው ርብርብም ወደ መርቱ ወደ 118 ሚሊዮን ኩንታል ከፍ ማለቱን አስረድተዋል፡፡
ከዚህ በፊት በኤክስቴንሽን ይሳተፍ የነበረው አርሶ አደር ከ300 ሺህ የማይበልጥ እንደነበርና በአሁኑ ወቅት ግን 3ነጥብ 6 ሚሊዮን አርሶዳር ተጠቃሚ አንደሆነ ገልፀዋል፡፡
አገሪቱ በግብርናው መስክ ላስመዘገበችው እድገት ክልሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦኦ ያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ወደፊትም ይህንን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በክልሉ የታየውን የግብርና ምርት እድገት ቀጣይነት ለማስመዝገብ የተለያዮ አካላት ርብርብ የሚያስፈለግ ያሳሰቡት የቢሮው ሃላፊ የምርምር ተቋማት እያካሔዱ ያለውን የግብርና ምርምር ለአርሶ አደሩ በማድረስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡
---END---