አዲስ አበባ, ጥቅምት 15 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - ቴክ ፋይቭ ኮንፈረንስ ኤንድ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ኢንተርፕራይዝ "ቶፕ ኢትዮጵያን ሞዴልስ" በሚል ስያሜ 15 ምርጥ ሞዴሎችን በመምረጥ በዱባይ፣ በጃፓንና በሌሎች ሃገራት የፋሽን ሾው ትርዒት እንደሚያቀርብ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ሚኒስቴሩ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ዝግጅቱ ኢትዮጵያን በውጪው ዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡
ምርጥ ሞዴሎቹ ወደተጠቀሱት ሃገራት ከመሄዳቸው በፊት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መሓሙዳ አህመድ እና ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት ጥቅምት 16 ቀን 2000 ዓ ም ከቀኑ 9 ሰዓት በደብረዘይት ኩሪፍቱ ሪዞርት የመጀመሪያ ትርዒታቸውን እንደሚያቀርቡ አስታውቋል፡፡
ሪ 4፡45 ያ4፡50የ4፡45
---END---