ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በድጋሚ በመመረጣቸው የፖላንድ ፕሬዚዳንት የደስታ መልዕክት አስተላለፉ ፡፡
አዲስ አበባ, ጥቅምት 13 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - የፖላንድ ፕሬዚዳንት ሌች ካችዚንስኪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በድጋሚ በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገለጹ ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቀው ፕሬዚዳንት ካችዚንስኪ በፖላንድ ሕዝብና መንግስት እንዲሁም በራሳቸው ስም በላኩት የደስታ መግለጫ ለፕሬዚዳንት ግርማ መልካም የሥራ ዘመን ተመኝተዋል ፡፡

ረጅም እድሜ ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነትና ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት መግለፃቸውንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል ፡፡

ሪ፡ 11፡10 ኤ2 11፡18 ጥጥ

---END---

Headlines
በዳርፉር የአፍሪካ ሕብረተና የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ተልዕኮን በቅረቡ መሉለሙሉ ለማሰማራት ሁኔታዎች መመቻቸቱን ተገለጸ
የአፍሪካን የንግድ እንቅስቃሴ የሚያስተዋውቅ ድረ ገጽ ተከፈተ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለአራት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ
ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በድጋሚ በመመረጣቸው የፖላንድ ፕሬዚዳንት የደስታ መልዕክት አስተላለፉ ፡፡
ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ወዳጅነቷን ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ታረጋግጣለች
የቤቶች ግንባታ ሥራዎች ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉት ለግንባታ የሚውለው ብሎኬት ጥራቱ የተጠበቀ ሲሆን ብቻ ነው
የኢጋድ ሁለት ኮሚቴዎች በቅድመ ግጭት አወጋገድ ላይ ያተኮረ የሦስት ቀናት ስብሰባ ካርቱም ላይ ያካሂዳሉ
በደቡብ ክልል በበልግ ወቅት ከለማው መሬት ከ41 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተገኘ
(c) The Ethiopian News Agency