የአፍሪካን የንግድ እንቅስቃሴ የሚያስተዋውቅ ድረ ገጽ ተከፈተ
አዲስ አበባ, ጥቅምት 13 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - ንግድና ኢንቨስትመንትን ወደ አፍሪካ ለመሳብ ብሎም የአህጉሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ በውስጥና በውጪ የሚያስተዋውቅ አዲስ ድረገጽ ተከፈተ፡፡

"www.opportunitiesinxfrica.com ደብሊው ደብሊው ደብሊው ዶት ኦፖርቹኒቲስኢንአፍሪካ ዶት ኮም" የተባለውና በአፍሪካ ያለውን የንግድ ሁኔታ የሚያስተዋውቀው ይህ ድረ ገጽ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ድጋፍ የተዘጋጀ ነው፡፡

ዌብሳይቱ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች በአህጉሪቱ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱና የንግድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ብሎም ከአህጉሪቱ ኩባንያዎች ጋር ጠንካራ የንግድ ግኙነት እንዲመሠርቱ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል ፡፡

የአፍሪካ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን በዓለም ገበያ እንዲሸጡም ያስችላል ተብሏል፡፡

ድረ ገጹ የአፍሪካ መንግሥታት በአገሮቻቸው ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች ፣ በየአገራቱ የሚገኙ ኩባንያዎች ምርቶችና አድራሻ፣ የሚያስተዋውቁበትና የሚሸጡበት ገጾችን ያካተተ ነው፡፡

ድረ ገጹ የአፍሪካ አገራትና ኩባንያዎች የንግድ አማራጮቻቸውን ፣ ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን ለመላው ዓለም እንዲያስተዋውቁ ተደርጎ መቀረጹን መቀመጫውን አየርላንድ ዱብሊን ያደረገው ኤች አር ኤ ኮሚዩኒኬሽንስ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ሪ-10፡05 ያ-10፡16 ኤ2 11፡39 ጥጥ

---END---

Headlines
በዳርፉር የአፍሪካ ሕብረተና የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ተልዕኮን በቅረቡ መሉለሙሉ ለማሰማራት ሁኔታዎች መመቻቸቱን ተገለጸ
የአፍሪካን የንግድ እንቅስቃሴ የሚያስተዋውቅ ድረ ገጽ ተከፈተ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለአራት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ
ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በድጋሚ በመመረጣቸው የፖላንድ ፕሬዚዳንት የደስታ መልዕክት አስተላለፉ ፡፡
ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ወዳጅነቷን ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ታረጋግጣለች
የቤቶች ግንባታ ሥራዎች ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉት ለግንባታ የሚውለው ብሎኬት ጥራቱ የተጠበቀ ሲሆን ብቻ ነው
የኢጋድ ሁለት ኮሚቴዎች በቅድመ ግጭት አወጋገድ ላይ ያተኮረ የሦስት ቀናት ስብሰባ ካርቱም ላይ ያካሂዳሉ
በደቡብ ክልል በበልግ ወቅት ከለማው መሬት ከ41 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተገኘ
(c) The Ethiopian News Agency