አዲስ አበባ, ህዳር 19 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የህዝቦች ዋስትና የሆነውን ህገመንግሥት በንቃት በመጠበቅ ማስመዘገብ የተጀመረው ዕድገት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ትኩረት የሚደረግበት ዕለት ሊሆን እንደሚገባ የኦሮሚያ ማስታወቂያና ህዝብ ግንኙነት ቢሮ አስታወቀ፡፡በቅርቡ የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን በማስመልክት ቢሮው ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጸው ህዳር 29 ቀን 1987 ዓም ፀድቆ ሥራ ላይ እየዋለ ያለው ህገ መንግሥት ለመላው የአገሪቱ ህዝቦች በፖለቲካ፣ በኤኮኖሚውና በማህበራዊ መስኮች መሠረታዊ ጥቅሞችን አስገኝቷል፡፡
ዕለቱ አዲሱ የኢትዮጵያ ሚሌኒየም እየተከበረ ባለበት ወቅት መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ገልጾ በሚሌኒየሙ ድህነትን ለማስወገድ፣ የበለፀገችና መልካም አስተዳዳር የሰፈነባት አገር ለመገንባት ቃል እንደተገባው ሁሉ ህገመንግሥቱን ከማንኛውም አደጋ ለመታደግም ዳግም ቃል የሚገባበት ዕለት ሊሆን ይገባል ብሏል፡፡
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በመሆን ሲታገሉለት የነበረው የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እውን የሆነበት ቀን መሆኑንም ገልጿል፡፡
የኦሮሞ ህዝብ እንደ ሌሎች የአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች የኢትዮጵያን ህገ መንግሥት ዕውን በማድረግ በተደረገው ትግል ውስጥ የራሱን ድርሻ የተወጣ ሲሆን ህገ መንግሥቱ ባስገኛቸው ድሎችም ተጠቃሚ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ህዳር 29 በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነት የተፈጠረበት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በመሆኑ የኦሮሞ ህዝብና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቀኑን በታላቅ አክብሮት እንደሚመለከቱትም አመልክቷል፡፡
በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ዕኩልነት የተረጋገጠበት ህገ መንግሥት በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሙሉ ፍላጎትና ተሳትፎ ከፀደቀ 13 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡
ስ 5፣00 ሪ 5፣45 ኤ 6፣06 ኤ6፡25 የ6፡32 ጥ ከ
---END---