ሕወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበት 33ኛው ዓመት በዓል በሽሬእንደስላሴ በክልል ደረጃ ይከበራል
ሽሬእንደስላሴ, ህዳር 17 ቀን 2000 (ሽሬ እንዳስላሴ) - ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የትጥቅ ትግል የጀመረበት 33ኛው ዓመት መታሰቢያ በዓል በሽሬእንደስላሴ በክልል ደረጃ ለማክበር የተለያየ ዝግጅት መጀመሩን የትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን መስተዳድር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ገለጠ፡፡

የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ ረዳኢ በዛብህ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት ሕወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበት 33ኛው ዓመት መታሰቢያ በዓል በሽሬእንደስላሴ በክልል ደረጃ የሚከበረው የክልሉ ሚሊንየም ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ነው፡፡

በዓሉን በድምቀት ለማክበር የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመው በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጠው በበዓሉ የፓነaል ውይይት፣ኤግዚቢሽንና ባዛር፣ስፖርትና ሌሎችም ዝግጅቶች መኖራቸውን አስታውቀዋል፡፡

በበአሉ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይን ለማጠናከር የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መወሰናቸውን አስታውቀው እስካሁንም የዞኑ ስምንት ወረዳ የካቢኔና ስራ አስፈጻሚ አባለaት ከደሞዛቸው ከ20 አስከ 30 በመቶ ለመስጠት መወሰናቸውን ገልጠዋል፡፡

ድህነትን በማስወገድ ሀገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ በተጀመረው ጥረት የክልሉ ሕዝብ የሚጠበቅበትን ድርሻ ለመወጣት በበዓሉ ቃል የሚገባበት መሆኑን ገልጠዋል፡፡

በዓሉ በዞኑ እንዲከበር የተወሰነው ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የትጥቅ ትግል የጀመረበት ደደቢት የተባለው አካባቢ የሚገኝበት በመሆኑ ጭምር እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

ሪፖያ10፡25 ኤዲ2 5፡30 ያለ 5፡40 ጥደ

---END---

Headlines
ሕወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበት 33ኛው ዓመት በዓል በሽሬእንደስላሴ በክልል ደረጃ ይከበራል
የዓለም ኤድስ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ በአማራ ክልል ይከበራል
በአፋር ክልል ከ1 ሺህ 600 በላይ ቆጣሪና ተቆጣጣሪዎች ወደምድብ ቦታቸው ተሰማሩ
ኢትዮጵያ ከቡናዋ ተገቢ ጥቅም እንድታገኝ ለመርዳት የእንግሊዙ ነጋዴ ወሰኑ
(c) The Ethiopian News Agency
㰊瑨汭㰾潢祤㰾楤⁶瑳汹㵥搢獩汰祡渺湯≥㰾晩慲敭猠捲∽瑨灴⼺洯獹祰楦敬⹳湣焯穡獷⽸湩敤⹸桰≰眠摩桴∽㈳∰栠楥桧㵴㈢〴㸢⼼晩慲敭㰾搯癩㰾戯摯㹹⼼瑨汭>