የኢትዮ-ኤርትራ ችግር በሰላም እንዲፈታ ኢትዮጵያ ለፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች ተግባራዊነት ምንጊዜም ዝግጁ ናት
አዲስ አበባ, ህዳር 4 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያና ኤርትራ በመካከላቸው ዘላቂ ሰላምን ለማውረድና ሁለቱ አገራት የደረሱበትን የአልጀረስ ሰላም ስምምነትያለምንም ቅድመ ሁኔታ ገቢራዊ እንዲያደርጉና በአካባቢው ሰላማዊ ሁኔታን እንዲፈጠር በሚደረገው ሂደት ውስጥ ሁለቱ አገራት በቁርጠኝነት እንዲንቀሳቀሱ ላቀረቡት ጥሪ ኢትዮጵያ አሁንም ዝግጁ ሆኗን አረጋገጠች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛሬ ማምሻውን የጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያና ኤርትራ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያወጡትን ሪፖርት በተመለከተ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ ውሳኔውን ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ በተደጋጋሚ መግለጿን በማስታወስ የድንበር ማካለሉ በአለም አቀፍ ህግና ስርአት እንዲተገበር ታግዛለች፣ ምንጊዜም ለሰላም ቆማለች ፡፡

የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሁለቱ አገራት ወታደራዊ ሃይልን ከመጠቀምና በመካከላቸው ያለውን ውዝግብ በሃይል ለመፍታት ከሚደረግ ማናቸውም ጠብ አጫሪ ተግባራት እንዲቆጠቡና በመካከላቸው ያለው ግንኙነት ሰላማዊና ክልሉም የተረጋጋ እንዲሆን ጥረት እንዲደረግ በማለት ላቀረቡት ጥሪ ኢትዮጵያ ምንጊዜም ለጥሪው ቀና ምላሽ እንደምትሰጥ አመልክቷል፡፡

የጸጥታ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት መግለጫ ኢትዮጵያና ኤርትራ በመካከላቸው ያለውን ግጭት ለመፍታት በአልጀርስ የደረሱበትን የሰላም ስምምነትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን የሰላም ሃሳብ ገቢራዊ እንዲያደርጉ ይጠይቃል፡፡

የፕሬዚዳንቱ መግለጫ በተጨማሪም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም አስከባሪ ተልእኮ /አንሚ/ በሁለቱ አገራት ድንበር አካባቢ ለሚያከናውናቸው የሰላም ማስከበር ተግባራት አስፈላጊውን እርዳታና እገዛ እንዲያደርጉ ያሳሰበ ሲሆን ኢትዮጵያም የአንሚ ተልእኮ የተሳካና የተቃና እንዲሆን ከዚህ ቀደም እንዳደረገቸው ሁሉ ተባብራና በቅርበት ለመስራት ዝግጁ እንደሆነች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በድጋሚ አረጋግጧል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ በቅርቡ ባወጡት ሪፖርት እንዳረጋገጡት ኤርትራ በሁለቱ አገራት የጸጥታ ቀጣና ውስጥ ወታደሮቿን አስርጋ በማስገባት የአልጀረሱን የሰላም ስምምነት ጥሳለች፡፡

ምክር ቤቱ በሁለቱ አገራት መካከል ሰላማዊ ግንኙነት እንዲመሰረትና ዘላቂ ትብብር እንዲኖር እንዲሁም የድንበር ማካለሉ ጉዳይ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንዲከናወን ያቀረበውን ጥሪ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያላትን ውዝግብ ዘላቂ እልባት እንዲያገኝና የድንበር ማካለሉ ጉዳይም እንዲፋጠን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብላ ታምናለች ብሏል ቃል አቀባዩ፡፡

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ የድንበር ማካለሉ ጉዳይ እንዲከናወን ለሚያደርጉት ያላሰለሰ ጥረትም ድጋፏን እንደምትሰጥና በሂደቱም አጀማመርና ከኤርትራ ጋር ያለው ያለመግባባት እልባት እንዲያገኝ በሚካሄዱ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች ሁሉ የተቻላትን ድጋፍ በመስጠቱ በኩል ያላትን ቁርጠኝነት ቃል አቀባዩ ገልጧል፡፡

ኤ፡ጥከ

---END---

Headlines
የኢትዮ-ኤርትራ ችግር በሰላም እንዲፈታ ኢትዮጵያ ለፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች ተግባራዊነት ምንጊዜም ዝግጁ ናት
(c) The Ethiopian News Agency
㰊瑨汭㰾潢祤㰾楤⁶瑳汹㵥搢獩汰祡渺湯≥㰾晩慲敭猠捲∽瑨灴⼺洯獹祰楦敬⹳湣焯穡獷⽸湩敤⹸桰≰眠摩桴∽㈳∰栠楥桧㵴㈢〴㸢⼼晩慲敭㰾搯癩㰾戯摯㹹⼼瑨汭>