የሐረሪ ክልል አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ከ172 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ
ሐረር, ነሐሴ 18 ቀን 1999 (ሀረር) - የሐረሪ ክልል አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ለዘንድሮ አመት ስራ ማከናወኛ ከ172 ሚሊዮን ብር በላይ በጀትአጸደቀ ።ጉባኤዉ በተጨማሪ የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅና የካቢኔ አባላት ሹም ሽር በማካሄድ ትናንት ተጠናቋል ፡፡

ጉባኤው የክልሉን አስፈጻሚ አካላት እንደገና ለማደራጀትና የብዙሐን መገናኛ ኤጀንሲን ለማቋቋም የወጡ አዋጆችን ጨምሮ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስናን ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጆችን መርምሮ አጽድቆአል፡፡

ለክልሉ ሆስፒታሎች የተመደበው 10 ሚሊዮን ብርም ጥራት ያለው ቀልጣፋ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት በቂ ባልመሆኑ የምክር ቤት አባላት በጉዳዩ ላይ በመወያየት ከመጠባበቂያ በጀት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግበት ጠቁመዋል፡፡

ጉባኤው የክልሉ የካቢኔ አባልና የህዝብ አደረጃጀት ባህልና ማህበራዊ ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘይዳን በክሪ ህዝብና መንግስት የጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃት አልተወጡም በሚል ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ አድርጐአል፡፡

በምትካቸው አቶ ኢማጅ እንድሪስ የባህልና ህዝብ አደረጃጀት ቢሮ ሃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን የትምህርትና አቅም ግንባታ ቢሮ በመለያየታቸው አቶ ረጋሳ ከፍያለው ከክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድርነታቸው በተጨማሪ የእቅም ግንባታ ቢሮን እንዲመሩ ተሹመዋል፡፡

አቶ ነቢል መሐመድም የትምህርት ቢሮ ሃላፊ እንዲሆኑ በምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምጽ ተወስኖ ጉባኤው በትናንትናው እለት ተጠናቋል፡፡

---END---

Headlines
የሚሌኒየሙ በዓል አፍሪካውያን ካለፈው ዘመን የተሻለ ሰላም፣ ነፃነትና ተባብረው በመስራት ከፍተኛ ውጤት ለማምጣት ጉልህ አስተዋጽኦ
የኢትዮጵያ ሚሌኒዬም በአል የአገሪቱን ብቻ ሳይሆን መላው አፍሪካን እስመልክቶ በአለም ሀዘብ ዘንድ ያለውን የተሳሳተ ግምት የሚያስቀይር ነው - ኒው አፍሪካ
የሐረሪ ክልል አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ከ172 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ
መንግሥት የውኃውን ክፍለ ኢኮኖሚ ለማሳደግ የሚያደርገው ጥረት በባለድርሻዎች መተደገፈ አለበት
(c) The Ethiopian News Agency
㰊瑨汭㰾潢祤㰾楤⁶瑳汹㵥搢獩汰祡渺湯≥㰾晩慲敭猠捲∽瑨灴⼺洯獹祰楦敬⹳湣焯穡獷⽸湩敤⹸桰≰眠摩桴∽㈳∰栠楥桧㵴㈢〴㸢⼼晩慲敭㰾搯癩㰾戯摯㹹⼼瑨汭>