ENA
 


ዜና
አዲስ አበባ ግንቦት 17/2005 የአፍሪካን ህዳሴ ለማረጋገጥና ለውጡዋን ለማብሰር ሕዝቦቹዋ በሚቀጥሉት ሃምሳ አመታት ፊታቸውን ወደ ልማት ማዞር እንደሚገባቸው የአህጉሪቱ መሪዎች ገለጹ፡፡
አዲስ አበባ ግንቦት 17/2005 የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት የጋዜጠኞችን መብት በማስከበር ረገድ የምሥራቅ አፍሪካ ጋዜጠኞች ማህበርን በመደገፍ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
አዲስ አበባ ግንቦት 17/2005 ረጅም ቁመናው ለሰማይ ቅርብ ያስመሰለው የደቡብ ሱዳኑ ተወላጅ ፑሮ ኦኬሎ ኦቦን ያገኘሁት በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ባንዲራና ለ50ኛው ዓመት የሕብረቱ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ማድመቂያ ልዩ ዝግጅት ባሸበረቀው የአዲስ አበባው መስቀል አደባባይ ነበር፡፡
አዲስ አበባ ግንቦት 17/2005 አፍሪካ ባለፉት ዓመታት የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች የመጣች ቢሆንም በአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ሽግግር ለማድረግ ተግዳሮቶች እንዳጋጠሙ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ገለጹ።
ደብረብርሃን 17/2005 በሰሜን ሸዋ ዞን የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የደብረብርሀን ቅርንጫፍ በተቋቋመ ስድስት ወራት ከ4 ሺ 800 በላይ የግል ድርጅት ሠራተኞች በማህበራዊ ዋስትና ታቅፈዉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማደረጉን ገለጸ፡፡
መቀሌ 17/2005 የግንቦት 20 ድል ሴቶች ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸው እንዲረጋገጥ ያስቻለ የመስዋአትነት ውጤት በመሆኑ የድሉን ውጤቶች ለመጠበቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የትግራይ ክልል የተለያዩ የስራ ሀላፊ ሴቶች አሳሰቡ።
አዳማ ግንቦት 17/2005 በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የቴከኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት በገበያ ላይ ተፈላጊና ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ከማፍራት አኳያ ሰፊ ክፍተት እንደሚታይባቸው የአስተዳደሩ ቴከኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኤጄንሲ ገለጸ።
ጎባ ግንቦት 17/2005 በባሌ ዞን ራይቱ ወረዳ ባለፉት አስር ወራት ከ26 ሺ በላይ በመውለድ የእድሜ ክልል የሚገኙ እናቶች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ገለጸ።
አዲስ አበባ ግንቦት 17/2005 የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ 22ኛው አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ ትናንት ማምሻውን በሶማሊያ ጉዳይ ላይ በስፋት ተወያይቶ ውሳኔዎችን አጸደቀ፡፡
አዲስ አበባ ግንቦት 17/2005 ግሎባል ፈንድ በኢትዮጵያ የኤች.አይ.ቪ እና የቲቪ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የቅዱስ ጴጥሮስ ቲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታወቀ፡፡