ENA
 


ዜና
አዋሳ ግንቦት 10/2005 የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ለመገንባት የላቀ አስተዋጾኦ ያለውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ስራን ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ገለጹ፡፡
አዳማ ግንቦት 10/2005 የግልና የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአገሪቱ የህዳሴ ጉዞ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችል ብቃቱ የተረጋገጠ የሰው ሃይል ማፍራት እንደሚጠበቅባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ማስጠበቅ ኤጄንሲ ገለፀ፡፡
አክሱም ግንቦት 10/2005 በትግራይ ማዕከላዊ ዞን በየአመቱ የሚካሄደው የገጠር ወረዳዎች የ4 አይነት የስፖርት ውድድር በውቅሮ ማራይ ከተማ ትናንት ተጀመረ ፡፡ የስፖርት ውድድር የታወቁና ሀገራችንን ሊያስጠሩ የሚችሉ ስፖርተኛች የሚመለመሉበት ነው ፡፡
አዋሳ ግንቦት 10/2005 በኦሮሚያ ክልል ከ1 ጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በበጀት ዓመቱ የተጀመሩ 259 የጤና ተቋማት ግንባታ በመፋጠን ላይ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
አሰላ ግንቦት 10/2005 በአርሲ ዞን የሥነ ተዋልዶና የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ በተካሄደው እንቅስቃሴ ከ300ሺ በላይ የሚሆኑ ሴቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን የዞኑ ጤና ጥበቃ መምሪያ አስታወቀ፡፡
ነገሌ ግንቦት 10/2005 በአርብቶ አደሩ አካባቢ የበልጉን ዝናብ ተከትሎ በእንስሳት ጤና ላይ ችግር እንዳይከሰት ከ621 ሺ ለሚበልጥ የቤት እንስሳት ክትባት መሰጠቱን የጉጂ ዞን እንስሳት ሀብት ገበያ ልማትና ጤና ኤጀንሲ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
አሶሳ ግንቦት 10/2005 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከግልገል በለስ ወደ አሶሳ የትራንስፖርት አገልግሎት እጥረት በመከሰቱ መቸገራቸውን ተገልጋዮች አመለከቱ፡፡
ማይጨው ግንቦት 10/2005 የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ሕግና ፍትህ አተገባበር ስርዓት ለማሻሻል በፍትህ አካላት የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡
አዲሰ አበባ ግንቦት 10/2005 በሽመና ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥማቸውን የግብዓት ችግር ለመፍታት የሚያስችል ውይይት መደረጉን የፌዴራል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
አዲስ አበባ ግንቦት 10/2005 በትግራይ ክልል ከ534 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የማይፀምሪ - ዲማ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ፡፡